Home / ዜና / ወቅታዊ / ኩዌት ለጉብኝት ቪዛ እና ለነዋሪነት ፈቃድ ባለቤቶች የቆይታ ጊዜ ማራዘሚያ ፈቀደች

ኩዌት ለጉብኝት ቪዛ እና ለነዋሪነት ፈቃድ ባለቤቶች የቆይታ ጊዜ ማራዘሚያ ፈቀደች

የካቲት 27/2018 (ገበያ ሚዲያ) በቀጠናው ካለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ለውጥ አንጻር የኩዌት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች እፎይታ የሚሰጡ ሁለት ዋና ዋና ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

የመጀመሪያው ውሳኔ የጉብኝት ቪዛ ለያዙና የቪዛ ጊዜያቸው ላለፈባቸው ወይም ሊያልቅ ለተቃረበባቸው ሰዎች ሁሉ የአንድ ወር የቪዛ ጊዜ ማራዘሚያ የሚሰጥ ነው።

ይህ ማራዘሚያ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ (e-System) በራሱ ጊዜ የሚታደስ በመሆኑ፣ ተጠቃሚዎች በአካል መገኘት እንደማያስፈልጋቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ለዚህ አገልግሎት የሚከፈል ምንም ዓይነት ክፍያም ሆነ የቆይታ ቅጣት እንደማይኖር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አረጋግጧል።

ሁለተኛው ውሳኔ ደግሞ የኩዌት ነዋሪ ለሆኑና በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውጭ ለሚገኙ ግለሰቦች የሚመለከት ሲሆን፤ የተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ ለተቃጠለባቸው ነዋሪዎች የሦስት ወር ተጨማሪ የጊዜ ማራዘሚያ ተሰጥቷቸዋል።

ይህም ማራዘሚያ ያለምንም ክፍያና በአካል መቅረብ ሳያስፈልግ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚከናወን ይሆናል ተብሏል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንደ አገሩ ወቅታዊ ሁኔታ እነዚህ የተቀመጡት የጊዜ ገደቦች ወደፊትም ሊራዘሙ እንደሚችሉ ጠቁሞ፤ ለማንኛውም ድንገተኛ አደጋ በ 112 ላይ በመደወል የፖሊስ፣ የእሳት አደጋ ወይም የሕክምና እርዳታ ማግኘት እንደሚቻል አሳስቧል።

#ገበያ_ሚዲያ#gebeyamedia#gebeyanews#ገበያ#Ethiopia#ኢትዮጵያ#addisababa#አዲስአበባ#kuwait#visa#VisaExtension#ResidencyPermit#kuwaitupdate#ኩዌት#ቪዛ#የመኖሪያፈቃድ#ቪዛማራዘሚያ#ወቅታዊመረጃ

Leave a Reply

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው